የህዝብና ቤት ቆጠራ መጋቢት 19 ይጀምራል

0
849

በኢትዮጵያ ለአራተኛ ጊዜ የሚካሄደው የህዝብና ቤት ቆጠራ መጋቢት 19 ቀን 2011 ዓ.ም በመላው አገሪቷ ይጀመራል።
በየአስር ዓመቱ ለሚካሄደው ለዚህ ስራ 152 ሺህ የቆጠራ ቦታዎች፣ 182 ሺህ ቆጣሪዎችና 38 ሺህ ተቆጣጣሪዎች እንደዚሁም ለቆጠራው የሚያመቹ የቆጠራ ቦታ ካርታዎች መዘገጀታቻዉን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎች ዘግቧል፡፡
ህዝቡ ትክክለኛውን መረጃ በመስጠት ለስኬቱ የበኩሉን ሚና መጫወት እንዳለበት ነው በኤጀንሲው የኦሮሚያ የህዝብና ቤት ቆጠራ ኮሚሽን ፀሃፊ አቶ ሼኮ ጉሩ አሳስበዋል።
የቆጠራው በትክክልና በጥራት መካሄድ የአገሪቱን ሁለንተናዊ ተጨባጭ ሁኔታ በማመላከት ከአገር ባሻገር ዓለም አቀፍ ፋይዳም ያለው በመሆኑ መረጃው በትክከል መሰብሰብ እንዳለበት ፀሃፊው ገልጸዋል።
በጎዳና ላይ የሚኖሩና ተፈናቅለው ወደየቄያቸው ያልተመለሱ የህብረተሰብ ክፍሎችን በያሉበት ለመቁጠር የሚያስችል የአሰራር ስርዓት መዘጋጀቱንም አስታውቀዋል።
አራተኛው የህዝብና ቤት ቆጠራ የሚካሄደው በዲጂታል ሳተላይት ስርዓት በመታገዝ ነው ያሉት አቶ ሼኮ፤ የአፋር ስምጥ ሸለቆን ጨምሮ ለዲጂታል ስርዓቱ አመቺ ባልሆኑ አንዳንድ የአገሪቱ ክፍሎች ቆጠራው የሚካሄደው ከዚህ በፊት በነበረው አሰራር መሆኑን ገልጸዋል።
(ምንጭ፡-ኢት/ፕሬስ ድርጅት)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here