ኩሪፍቱ ሆቴል በሰመራ ስራ ጀመረ

0
918

ኩሪፍቱ ሪዞርት እና ስፓ በሰመራ ከተማ የሚታየውን ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎች እጥረት ለማቃለል 5ተኛ ቅርንጫፉን አፋር ላይ አድርጓል።
በአፋር ክልል በርካታ የሚጎበኙ ተፈጥሮአዊ መስህቦች ቢኖሩም ለሚመጡት ቱሪስቶችና ጎብኚዎች የሚሆን በቂ ማረፊያ ግን እስካሁን የለም።
የዳሎልን ስምጥ ሸለቆ፣ የማይሞተውን ቮልካኖ፣ አሎሎባድ፣ እንዲሁም አፍዴራን እና የተለያዩ የአጥንት ቅሪቶች ለማጥናት ወደ ስፍራው የሚያቀኑ ሰዎች በቂ ማረፊያ ሳያገኙ እንደሚቸገሩ በመገንዘብ ነው።
በአፍሮ ጽዮን ኮንስትራክሽን ባለቤትነት የተያዘውን ሆቴል ለማስተዳደር ሃላፊነቱን የወሰደው በቢሾፍቱ፣ ባህርዳር፣ በናዝሬት እና በጅቡቲ ካለው ሪዞርት ቀጥሎ 5ተኛ እንደሆነ የተነገረለት ኩሪፍቱ 148 ክፍሎችን ሲያካትት ከእነዚህም 4ቱ ፕሬዚዳንሺያል የሚሰኙ ስዊት ክፍሎች ናቸው።
የተሟላ የስፓ፣ መዋኛ ገንዳ፣ ሁለት 1000 ሰዎችን ማስተናገድ የሚችሉ የስብሰባ አዳራሾችን፣ የጌጣጌጥ መሸጫዎችን አካቶ ለየት ባለ መንገድ የቴኒስ መጫወቻ ሜዳ ጨምሮ ሰመራ ላይ ከትሟል።
500 ሚሊየን ብር ወጪ የወጣበት ይህ ሪዞርት ለቀሪ ጉዳዮች 100 ሚሊየን እንደሚፈልግ የተነገረ ሲሆን የተፈጥሮው የሆት ስፕሪንግ ስፓ ሲጀመር ተጨማሪ የቱሪስት መስህብ ይሆናል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here