ኢትዮጵያ የጤፍ ባለቤትነቷን እንዴት ተነጠቀች…?

0
649

በአውሮፓ ሃገራት ላይ የጤፍ ምርቶች ባለቤትነቷን የተነጠቀችው ኢትዮጵያ ከአንድ ድርጅት ጋር ባደረገችው ስምምነት ምክንያት ነው።
ከአስርት ዓመታት በፊት ኢትዮጵያ ‘ሄልዝ ኤንድ ፐርፎርማንስ ፉድ ኢንተርናሽናል’ ከተባለ የሆላንድ ድርጅት ጋር በአውሮፓ ላይ የጤፍ ምርትን ለማሳደግና የቴክኖሎጂ ሽግግርን ከግምት ውስጥ በማስገባት ስምምነት ተፈራርማ ነበር።
ስምምነቱ በኦስትሪያ፣ ቤልጂየም፣ እንግሊዝ፣ ጣልያንና ሆላንድ የጤፍ ምርቶች ላይ ያላትን መብት የነጠቃት ሲሆን የኢትዮጵያ መንግሥትም የባለቤትነት መብቱን ለማስጠበቅ ለ15 ዓመታት ሲታገል ቆይቷል።
ውዝግቡን የበለጠ ግራ አጋቢ ያደረገው ነገር ደግሞ ከኢትዮጵያ ጋር የተፈራረመ ድርጅት ‘ሄልዝ ኤንድ ፐርፎርማንስ ፉድ ኢንተርናሽናል’ የሚባል ድርጅቱ መፍረሱ ነው።
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ በትዊተር ገፃቸው፥ ኢትዮጵያ ክስ ለመመስረት ዝግጅቷን ማጠናቀቋን አሳውቀዋል።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልእክተኛ አምባሳደር ታየ አፅቀሥላሴ በበኩላቸው በትዊተር ገፃቸው ላይ እንዳሰፈሩት ይህ ጉዳይ ለረጅም ጊዜ እየተጓተተ ያለ መሆኑን ጠቅሰው፤ ኢትዮጵያ ቡናን ለማስመዝገብ በሄደችበት መንገድ ምርጥ የሚባል ጠበቃዎች ሊወክሏት እንደሚገባ አስረድተዋል።
Via: BBC News Amharic

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here