ምክር ቤቱ የሲጋራ ማጨሻ ስፍራን የሚገድብና አልኮልን በብሮካስት ሚድያ ማስተዋወቅ የሚከለክውን አዋጅ አፀደቀ

0
470

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሲጋራ ማጨሻ ስፍራን የሚገድብና አልኮልን በብሮካስት ሚድያ ማስተዋወቅ የሚከለክውን አዋጅ አፀደቀ።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው እለት ባካሄደው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 24ኛ መደበኛ ስብሰባው ነው አዋጁን ያፀደቀው።
ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው የሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የምግብና መድኃኒት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ያቀረቡትን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብን ተመልክቷል።
የምክር ቤቱ አባላትም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያዩ በኋላም አፅድቀውታል።
በዛሬው እለት በፀደቀው አዋጅ ላይም መስሪያ ቤቶች፣ ጤና ተቋማት እና የወጣቶች መዝናኛ በሚገኙባቸው አከባቢዎች 100 ሜትር ርቀት ውስጥ ሲጋራ ማጨስ ክልል መሆኑ ተደንግጓል።
ማንኛውንም የአልኮል ምርት በብሮድካስት ሚድያ ማስተዋወቅ የሚቻለውም ከምሽቱ 5 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት ብቻ እንዲሆን አዋጁ ደንግጓል።
በተጨማሪም ከአልኮል መጠጦች ጋር በተያየዘም ከ21 ዓመት በታች ለሆኑ ታዳጊዎች አልኮል መሸጥ ክልክል መሆኑም ተገልጿል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here