ቤተ እስራኤላዊያንን የጫነ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ አውሮፕላን ወደ እስራኤል ተጓዘ

0
536

እ.አ.አ 2015 በተላለፈው ውሳኔ መሰረት ቀሪ 9ሺህ ቤተ-እስራኤላውያን ከቤተሰቦቻቸው ጋር መልሶ ለማገናኘት በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ፡፡
መንግስት ለ1000 የቤተ እስራኤላዊያን በእስራኤል ከሚገኙ የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲገናኙ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት ከአፍሪካ የመጡ የመጀመርያዎቹ 80 ተጓዦች ሰኞ ቤንግርዮን አየር ማረፍያ ይደርሳሉ፡፡
እስራኤል ሲደርሱ የአይሁድ ኤጀንሲ ሊቀመንበር በሆኑት አይዛክ ሀርዞክ ስደተኞችን በመጀመርያ ተርሚናል አቀባበል ይደረግላቸዋል፡፡
የመታወቅያ ካርዳቸው ከተቀበሉ በኋላ ቤተሰቦቻቸው ወደ ሚጠብቋቸው እንግዳ ማረፊያ ያመራሉ ተብሏል፡፡
በመቀጠልም ቤተስራኤላዊያኖቹ የሚየስፈልጉ መስፈርቶችን በማሟላት በእስራኤል አዲስ ህይወት እንደሚጀምሩ ይደረጋል ተብሏል፡፡
በህዳር 2015 መንግሥት ወደ እስራኤል ከተጓዙት ስደተኞች ቀሪዎቹ 9 ሺህ ቤተ እስራኤላዊያን ዳግም ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለማገናኘት ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወቃል፡፡
በ2017 መገባደጃ ላይ 1ሺህ 300 የሚሆኑ ወደ አገሪቱ እንዲገቡ የተደረገ ሲሆን ቀሪ 8 ሺህ አካባቢ የሚሆኑ በኢትዮጵያ ቀርተው ነበር፡፡
በጥቅምት 2018 መንግስት ሌሎች 1ሺህ የሚሆኑ ከቤተሰቦቻቸው በእስራኤል የሚገናኙት የመጀመርያ ዲግሪ ያላቸው ዜጎቹን ወደ እስራኤል ለማምጣት ወስኗል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here