የቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ መታሰቢያሐውልት በአፍሪካ ሕብረት ጊቢ ውስጥ ከቀናት በኋላ ይቆማል ተባለ፡፡

0
648

32ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ከጥር 30 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነብያት ጌታቸው በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ የህብረቱ የመሪዎች ጉባዔ ከጥር 30 እስከ የካቲት 4 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።
በዚህም መሰረት የአፍሪካ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ከጥር 30 እስከ የካቲት 1 ቀን 2011 ዓ.ም ይካሄዳል ብለዋል።
የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ደግሞ የካቲት 3 እና 4 ቀን በአዲስ አበባ እንደሚካሄድም ቃል አቀባዩ ገልፀዋል።
32ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ የስደተኞች እና የውስጥ ተፈናቃዮች ጉዳይ ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚወያይም ነው ቃል አቀባዩ ያስታወቁት።
ቃል አቀባዩ አያይዘውም በጉባኤው ወቅት በአፍሪካ ህብረት ቅጥር ግቢ ውስጥ የቆመው የአፄ ኃይለስላሴ ሐውልት በይፋ እንደሚመረቅም ተናግረዋል።
የአፄ ኃይለስላሴ ሐውልት በኢትዮጵያ መንግስት ወጭ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀ ሲሆን፥ በ32ኛው የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ መክፈቻ ላይ በህብረቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለእይታ በሚመች ቦታ ላይ እንዲቆም ተደርጎ በይፋ ይመረቃል ብለዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here