አትሌት ደራርቱ ቱሉ የአድዋን ድል ለመዘከር በባዶ እግሯ 500 ሜትር ልትሮጥ ነው

0
867

የአድዋ ድልን የሚዘክር የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በአዲስ አበባ የካቲት 24 ቀን 2011 ዓ.ም ሊካሄድ ነው።
የውድድሩ የክብር አምባሳደር የሆነችው አትሌት ደራርቱ ቱሉ በጎዳና ሩጫው ላይ እንደምትሳተፍ ገልጻለች።
”ለመጨረሻ ጊዜ በውድድር የተሳተፍኩት ከስምንት ዓመታት በፊት ነው፤ ከሁለት ዓመት በፊት በህዳሴው ግድብ ሩጫ ተሳትፎ ነበረኝ፤ ለአድዋው ሩጫ ልምምድ ሰርቼ 9 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትሩን በጫማ የተቀረውን 500 ሜትር በባዶ እግሬ ለመሮጥ ቃል እገባለሁ” ብላለች።
የውድድሩ አምባሳደር ሆና በመመረጧ ከፍተኛ ኩራትና ክብር እንዲሁም እድለኝነት እንደሚሰማት ለኤዜአ ተናግራለች።
በአድዋ ድል እናቶችና አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው ያቆዩትን ታሪክና ጀግንነት ሁሉም በተሰማራበት መስክ ውጤታማ በመሆን በስራው ጀግና መሆን እንዳለበትነው የጠቆመችው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here