15ሺህ የውጭ ሀገር ዜጎች ጥምቀትን በጎንደር ይታደማሉ፡፡

0
439

በመጭው ቅዳሜ የሚከበረውን የጥምቀት በዓል ለማክበር የውጭ ሀገራት ጎብኝዎች ወደ ጎንደር ከተማ እየገቡ ይገኛሉ።
ለዚህም ቀድመው የተመዘገቡ 17 የአውሮፕላን በረራዎች ወደ ከተማዋ እንደሚደረጉ ከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል።
በአጠቃላይ 15ሺህ የውጭ ሀገር ጎብኝዎች ይመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የጎንደር ከተማን ሀይማኖታዊና ታሪካዊ ክዋኔዎች እንዲሁም ታሪካዊ ቅርሶችን ለመጎብኘት 58 ሺህ 828 የውጭ ሀገር ቱሪስቶች በዓመቱ ይጎበኛሉ።
ባለፉት ወራት የጎንደር ከተማን ከጎበኙ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ጎብኝዎች 3 ሚሊዮን 230 ሺህ 593 ብር ገቢ መገኘቱን ከከተማ አስተዳደሩ ባህል ቱሪዝም ስርዓት መምሪያ  መረጃ ያመለክታል።

#አማራ ብዙሀን መገናኛ ድርጅት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here