“የቃቄ ውርድወት” ትውፊታዊ ተውኔት የመድረክ ቆይታውን አጠናቀቀ፡፡

0
788

“የቃቄ ውርድወት” ትውፊታዊ ተውኔት የመድረክ ቆይታውን አጠናቀቀ፡፡
ላለፉት ሶስት ዓመታት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ ላይ የቆየው “የቃቄ ውርድወት” ትውፊታዊ ተውኔት የመድረክ ቆይታውን ቅዳሜ ጥር 04 ቀን 2011 ዓ.ም አጠናቀቀ፡፡
ትውፊታዊ ተውኔቱ ከአንድ መቶ ሃምሳ ዓመት በፊት ከጉራጌ ህዝብ መካከል በመነሳት በሰላማዊ የትግል መንገድ የሴት ልጅን ሰብዓዊ ክብርና መብት ለማስከበር ጠንካራ እንቅስቃሴ በማድረግ በአህጉራችንና በዓለም አቀፍ ታሪክም በቅድሚያ ጉልህ ድርሻ ባላት የቃቄ ውርድወት ድንቅ ታሪክ እንዲሁም በቀደምት የጉራጌ ባህልና ስነ-ቃል ላይ አተኩሯል፡፡
ከትርኢቱ መጠናቀቅ በኋላ ለደራሲው፣ ለአዘጋጁ፣ ለረዳት አዘጋጁ፣ ለዝግጅት አስተባባሪዎች፣ ለጉራጌ የባህልና ልማት ማህበር፣ ለአንጋፋ አርቲስቶች፣ ለተዋንያን፣ ለመድረክ እነጻ ባለሙያዎች፣ ለአልባሳትና ቁሳቁስ ባለሙያዎች፣ ለመብራት ባለሙያዎች፣ ለድምጽ ቴክኒክ ባለሙያዎች፣ ለደንበኞች አገልግሎትና ለዲዛይነር የሰርተፊኬትና የአበባ ስጦታ ተደርጎ ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡

ምንጭ ፦የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here