አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ የሙዚቃ ኮንሰርት ማዘጋጀቱን አስታወቀ

0
620

አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ “ኢትዮጽያዊነትን እናወድስ” በሚል መሪ ቃል ታላቅ የሙዚቃ ኮንሰርት ማዘጋጀቱን አስታወቀ።
የሙዚቃ ኮንሰርቱ የፊታችን ጥር 12 በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ እንደሚቀርብ ተገልጿል።
ጉዳዩን አስመልክቶ የአዘጋጅ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ቸኮል ጌታሁን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫውም ኮንሰርቱ ኢትዮጽያዊነትን የማወደስንና ድርጅቱን በመላው ሀገሪቱ ለማደራጀት የሚያስችል ገቢን የማሰባሰብ አላማ የያዘ ነው ብለዋል።
በኮንሰርቱ ላይ ታዋቂ የሙዚቃ ባንዶች፣ ወጣትና አንጋፋ ድምጻውያን ይሳተፋሉ ተብሏል።
የመግቢያ ዋጋው ለመደበኛ 300 ብርና ለቪአይፒ 500 እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
አባላቱ፣ ደጋፊዎቹና መላው ሀገር ወዳድ የዝግጅቱ ተሳታፊ በመሆን ድጋፉን እንዲያሳይ የዝግጅት ኮሚቴው ጥሪውን አቅርቧል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here