ከመለየት ክፉ ነው እስከ ሲያምሽ ያመኛል/ተወልደ በየነ (ተቦርነ)

0
808

ተወልዶ ያደገው አዲስ አበባ መርካቶ ሰባተኛ 11 ቀበሌ ነው ።የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በየካቲት 23 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በኮልፌ ሁለተኛ ደረጃ አጠናቋል።
ለሙዚቃ በነበረው ፍቅር ትምህርት ቤት ሆኖ የአክሊሉ ስዩምን “መለዬት ክፉ ነው” ፣የቴዎድሮስ ታደሰን “ሳዱላዬ ነይ” በ ዕረፍት ስዓት ተማሪዎችን ከሚያዝናናባቸው ዜማዎች ጥቂቶቹ ነበሩ ።ቀጥሎ በቀይመስቀል አማካኝነት ወደ ተሰባሰበ የሙዚቃ ቡድን በመቀላቀል የአምስት ወር ግልጋሎት ሰጠ። ከዚያም
1_ድምፃዊ አብነት አጎናፍር
2_ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን
3_ድምፃዊ ና ሙዚቀኛ ይስማለም በርጋ
4_ድምፃዊት መስከረም ማሞ
5_የፊልም ባለሙያ ኤርሚያስ ሙሉጌታ
6_የፊልም ፀሀፊ አክሊሉ ኃይለማሪያም
7_ድምፃዊ ተስፉ እና ታሪኩ በርታን ባሰባሰበው መስታወት የሙዚቃ እና የቲያትር ክበብ በመግባት ሙያውን አሻሻለ። በአንጋፋው የዜማና ግጥም ደራሲ እንዲሁም ሙዚቀኛ አየለ ማሞ አሰባሳቢነት በተቋቋመው ክስታኔ ባንድም ለአንድ አመት አገልግሏል።ቀጣይ የሙያ ጉዞዉን ወደ ሸዋ ጌጥ የምሽት ክለብ አደረገ።
በዚህ የምሽት ክለብ ቆይታው በድምፃዊው ድንቅ ተሰጥኦ በተደነቀው አንጋፋው የዜማና ግጥም ደራሲ እንዲሁም የሙዚቃ አቀናባሪ አበበ መለሰ እገዛ የመጀመሪያ አልበሙን “ሶፊ እንዳትቀጠፊ”ን አሳትሞ ለህዝብ አቀረበ። በዚህ የመጀመሪያ አልበሙ የተካተቱት ሥራዎች በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ባያገኙም የድምጻዊዉን ድንቅ ችሎታ ግን አመላካች ነበሩ ።
አንድ ቀን በሸዋጌጥ የምሽት ክለብ ይሰሩ ከነበሩ ድምፃውያን አንዱ የነበረው ወዳጄ አማኑኤል መነኪል (አሚኮ) ለኢትዮጵያው የሙዚቃው ንጉሥ ጥላሁን ገሠሠ ያለኝን የተለየ ፍቅር ግምትውስጥ በማስገባት “እኛ ጋር ጎበዝ ድምፃዊ አለ ።የጥላሁንን ጥሩ አድርጎ የሚዘፍን እስቲ መተህ እየው” አለኝ እኔም ግብዣውን ተቀብዬ ወደ ሸዋጌጥ አቀናሁ።
እውነትም አንድ ቅብጥብጥ ወጣት መድረኩን እና ታዳሚውን በሚገባ ተቆጣጥሮ በሚገርም ብቃት የንጉሱን ተወዳጅ ዜማዎች “እኔም ሄድኩኝ ትቻት ብዬ ደህና እደሩ”ን እና “የጠላሽ ይጠላ” በሚገርም ብቃት አቀነቀነ። ገደብ በሌለው አድናቆት እና ግርምት እጄ ውሀ እኪቋጥር በማጨብጨብ ፍቅሬን ገለፅኩ ።
ይህ አድናቆት እና ፍቅር የወዳጅነት ስንቅ ሆኖ ላለፉት ሀያ አመት ይዞን ዘለቀ።ያ ለመጀመሪያ ጊዜ እጄ ውሀ እስኪቋጥር ያጨበጨብኩለት የኔ ዘመን ድንቅ ባለ ተሰጥኦ ከትውውቃችን ሁለት አመት በኃላ በ1992 ቴክ ፋይፍ በሚል መጠሪያ
1_ከበዛወርቅ አስፋው
2_ከአለማየሁ ሄርጶ
3_ትዕግሥት በቀለ
4_ኤልሳቤጥ ተሾመ ጋር በጋራ
ከ አለማየሁ ሄርጶ ጋር ኢቫንጋዲን
በግሉ ሳታመሀኝ ብላ የሚሉትን አልበሞች አሳትሞ የመጀመሪያ አድናቆቴ እውነት እንደ ሆነ መላው የሙዚቃ አፍቃሪው አረጋገጠልኝ። ከሳታመሀኝ ብላ የሙዚቃ አልበሙበኃላ እና በፊት
ቀጣዮቹን ነጠላ ዜማዎች በጋራና በግል አቀንቅኗል
1_ድሬ ድሬ
2_ማለባበስ ይቅር (ለኤችአይቪ በጋራ)
3__ባላገሩ ቁጥር 3(ከኤፍሬም ጋር በጋራ)
4__ወገን ተሰብሰብ
5_ለታናሿ ልስጋ
6_አሽከርክር ረጋ ብለህ (በጋራ)
7_አደራ (ከማሀሙድ ጋር በጋራ)
8_ወይን ያስተፈስህ ልበ ሰብ
9_አለቃዬ
10_ሰኔ
11_ላሊበላ
12_የግድ ነው
13_ለአባይ ወይስ ቬጋስ ፊልም ማጀቢያ
14 _ለቃልኪዳን ፊልም ማጀቤያ
በመጨረሻም ከ11 አመት በኃላ ከኔ ዘመን ባለድንቅ ተሰጥኦዎች ከጥቂቶቹ አንዱ የሆነው ድምፃዊ ጎሳዬ ተስፋዬ በአዲስ የሙዚቃ አልበም “ሲያምሽ ያመኛል” ብሎ መጥቷል። በነገራችን ላይ እኔና ጎሳዬ በሙያም በወዳጅነትም ካለፍንባቸው ያለፉት ሀያ አመታት እኔ ያልተሳተፍኩበት የጎሳዬ የሙዚቃ አልበም “ሲያምሽ ያመኛል” ብቻ ነዉ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here