ኢትዮጵያ ውስጥ የታሰረ አንድም ጋዜጠኛ የለም – ሲ.ፒ.ጄ

0
665

ኢትዮጵያ ውስጥ የታሰረ አንድም ጋዜጠኛ የለም – ሲ.ፒ.ጄ

ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ኮሚቴ (ሲ.ፒ.ጄ) ኢትዮጵያ ውስጥ ከ14 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የታሰረ ጋዜጠኛ አለመኖሩን አስታወቀ።

ኮሚቴው የፈረንጆቹን 2018 መጠናቀቅ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት ታግደው የነበሩ ከ260 በላይ ድረ-ገፆችን ክፍት ማድረጉንም ገልጿል።

ታስረው የነበሩ ጋዜጠኞች ትናንት በተገባደደው ዓመት መንግስት በወሰደው እርምጃ ሙሉ በሙሉ መፈታታቸውን ያስታወሰው ሲ.ፒ.ጄ እ.ኤ.አ. ከ2004 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ አንድም ጋዜጠኛ ያልታሰረባት አገር ሆናለች ብሏል።

መቀመጫውን በኒውዮርክ ያደረገው ኮሚቴው፣ ከዚህ ቀደም በጋዜጠኞች አያያዝ ዙሪያ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ተደጋጋሚ ክስ ያቀርብ እንደነበር አይዘነጋም።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here