የአርቲስት ይሁኔ በላይ እና መሀሪ ደገፋው ‹‹ፍቅር ያሸንፋል ተጓዥ ኮንሰርት›› ታህሳስ 27/2011ዓ.ም በጎንደር ይጀምራል

0
850

አርቲስት ይሁኔ በላይ እና መሀሪ ደገፋው ባሕር ዳር ገብተዋል

አርቲስቶቹ ባሕር ዳር ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ፣አድናቂዎቻቸው እና ቤተሰቦቻቸው አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡አርቲስቶቹ ከዓመታት በውጭ ሀገር ቆይታ በኋላ ነው  ባሕርዳር የገቡት፡፡

አርቲስት ይሁኔ በላይ ባለፉት ሶስት ዓመታት በስደት በነበረበት ጊዜ በህብረተሰቡ ላይ ይደርስ የነበረውን ችግር በሙዚቃ ለለውጡ የበኩሉን አበርክቷል፡፡ ‹‹ጥበብ ትልቅ ህይል ነው፡፡ አገር ይገነባል አገር ያፈርሳል፡፡›› ብሏል አርቲስት ይሁኔ፡፡
አርቲስት መህሪ ደገፋው የጥበብን ሀያልነት ሲናገር ‹‹ሙዚቃ ሀዘንን እና ደስታን መግለጫ ነው ፡፡ በመሆኑም በማህበረሰቡ ላይ ሲደርስ የነበረውን ችግር እኔም እንደ አንድ ዜጋ ጥበብን በመጠቀም ሃሳቤን ገልጫለሁ ፡፡ ጊዜውን ባላውቅም ለውጡ እንደማይቀር አስብ ነበር፡፡›› ብሏል፡፡
አርቲሰቶች በቀጣይ ‹‹ፍቅር ያሸንፋል ተጓዥ ኮንሰርት›› ዝግጅት ላይ ይሳተፍሉ ፡፡
የሙዚቃ ዝግጅቱ የሚካሄደው ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ በክልሉ ብሎም በሀገሪቱ ተከስቶ በነበረው ችግር ተቀዛቅዞ የቆየውን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ በኪነ ጥበቡ ዘርፍ ንቅናቄ ለመፍጠር ነው፡፡
ዝግጅቱ ታህሳስ 27/2011ዓ.ም በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ በመጀመር በአማራ ክልል በሚገኙ ታላላቅ ከተሞች ይካሄዳል፡፡ ከክልሉ ውጭም አዲስ አበባን ጨምሮ በሌሎች የክልል ከተሞችም ይካሄዳል ፡፡
አርቲስቶቹ ዝግጅቱን ለማካሄድ ታህሳስ 18/2011 ዓ.ም ነው አዲስ አበባ የገቡት፡፡

ምንጭ:- አማራ ብዙሀን መገናኛ ድርጅት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here