የአርቲስት ፍቃዱ ተከለማርያም መታሰቢያ ሃውልት ዛሬም ድረስ አልተሰራም።

0
552

አርቲስት ፍቃዱ ተከለማርያም ህይወቱ ካለፈ በርካታ ወራት ቢቆጠሩም፣ ሃውልቱ ግን ዛሬም አልተሰራም።

ወደ ቅዱስ ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ጎራ ያሉ የአይን እማኞች  በአርቲስቱ የመቃብር ስፍራ ላይ ምንም አይነት መታሰቢያ ሃውልት አለመቆሙን እየገለጹ ይገኛሉ።

የፍቃዱ ቤተሰቦች ደግሞ ” በስሙ የተሰበሰበውን ገንዘብ በተደጋጋሚ ጠይቀን ተስፋ ቆርጠን እሚሆነውን እያየን ነው፤ሌላው ገንዘብ ይቅር ለዚህ ታላቅ አርቲስት ሃውልት እንዲሰራ በተደጋጋሚ የጠየቅናቸው ሲሆን ሁሉም የናቴ መቀነት አደናቀፈኝ አይነት ሰበብ እየሰጡ ይኸው ሰባት ወራት አለፉ እንግዲህ ከማዘንና ከመቆጨት ውጪ ምንም አማራጭ ስለሌለን የእርሱን ምስል የያዘ ባነር አሳትመን ሰሞኑን ሃውልቱ መቆም እነበረበት ቦታ ላይ አስቀምጠናል አቅማችን የፈቀደው ይሄን ነው ታዲያ ከዚህ ውጪ ምን ማድረግ እንችላለን ? ለፍቄ ይሄ አይገባውም…” ማለታቸው ተሰምቶል

ከአገር ውስጥም ከውጭም ከ 4 ሚሊዮን ብር በላይ ፣ ፍቃዱ የታመመ ሰሞን መሰብሰቡና ይኸው ገንዘብም በግለሰቦችና “በኮሚቴ” እጅ እንደሚገኝ ይታወቃል።

ታዲያ የአርቲስት ፈቃዱን ሃውልት ማሰራት ያለበት ማነው? ይህን ያህል ጊዜስ ሳይሰራ ለመቆየቱ ምክንያቱ ምንድነው?

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here