የ71 ዓመቱ ፈረንሳዊ በበርሜል የአትላንቲክ ውቅያኖስን ሊያቋርጡ ነው

0
512

የ71 ዓመቱ ፈረንሳዊ ጃን ጃኩዬስ ሳቪን ግዙፉን የአትላንቲከ ውቅያኖስ በበርሜል ለማቋረጥ ተዘጋጅተዋል፡፡

ሞላላ ቅርጽ ያለውና ከበርሜል የተዘጋጀው ጀልባ መተኛ፣ ምግብ ማብሰያና ማከማቻ ያካተተ ነው ተብሏል፡፡በርሜሉ 3 ሜትር ርዝመትና 2 ነጥብ 10 ሜትር ስፋት እንዲሁም 7 ጫማ ስፋት ያለው ክፍል ያለው ሲሆን በተደጋጋሚ የሚያጋጥምን ማዕበል ለመቋቋም እንዲያስችል ሆኖ ተዘጋጅቷል ፡፡በበርሜሉ ወለል መሀል ላይ የአሳዎችን እንቅስቃሴ ማሳየት የሚያስችል ክፍተት እንደተዘጋጀለትም ተጠቁሟል፡፡

ግለሰቡ የአትላንቲክ ውቅያኖስን ለማቋረጥ ከስፔኗ ካናሪ ደሴት መነሻቸውን የሚያደርጉ ሲሆን በሶስት ወራት ውስጥ ካሪቢያን ለመድረስ አቅደዋል፡:

ጃን ጃኩዬስ ሳቪን በአሁኑ ወቅት ያለው የአየር ሁኔታ የተመቸ መሆኑን ገልጸው፥ እስከ መጭው እሁድ ድረስ የንፋሱ ሁኔታ የተሻለ እንደሚሆንም ተናግረዋል።

በበርሜል አትላንቲክን የሚያቋርጡት ግለሰብ ለፎቶ ባለሙያዎች የሚረዳ ምልክት እያስቀመጡ ለመሄድ ማቀዳቸውን እንዲሁም የጉዞውን ሂደት በየወቅቱ በፌስቡክ ለተከታታዮቻቸው እንደሚያደርሱም ነው የሚጠበቀው፡፡

ምንጭ፡-france24

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here