ሲኒማ ኢትዮጵያ ለመዘጋት ጫፍ ላይ ደርሻለሁ አለ፡፡

0
424

እድሜ ጠገቡ፣ በቅርስነትም የተመዘገበው ሲኒማ ኢትዮጵያ ለመዘጋት ጫፍ ላይ ደርሻለሁ አለ፡፡
እነ ማዘር እንዲያ፣ ዋክት፣ የቴክስ እና የአውሮፓ ሌሎችንም ፊልሞችን ሲያስኮመኩም እድሜውን የፈጀው ሲኒማ ኢትዮጵያ ለመዘጋት ከቋፍ አድርሶኛል ያለው ቀድሞ ከምከፍለው ወርሃዊ 7 ሺህ ብር የቤት ኪራይ አሁን መቶ ሰባ ዘጠኝ ሺሀ ብር ክፈል የሚል ደብዳቤ ስለደረሰኝ ነው ብሏል፡፡
የሲኒማ ቤቶች አስተዳደር ይሄ እንደ ቅርስ ሊጠበቅ የሚገባው ቤት በአነስተኛም ዋጋ ሰዎች አላስፈላጊ ቤት እንዳይሄዱ የሚያግዝ ስለሆነ የሲኒማ ኢትዮጵያ ነገር ጭማሪው ያሳስባል ብሏል፡፡
አቶ ጌታቸው ዘሩ የሲኒማ ቤቶች አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ የከተማ አስተዳደሩ እና የሚመለከታቸው ጉዳዩን ዳግም መመልከት አለባቸው ማለታቸውን ለሸገር ነግረዋል፡፡
አምባሳደርንና ሲኒማ ኢምፓየርንም በተመለከተ እስካሁን የመጣልን ደብዳቤ የለም ያሉት የስራ ሀላፊው ሲኒማ ኢትዮጵያ ላይ ግን የተደረገው ጭማሪ በአጭሩ ዝጉት ማለት ነው ብለዋል፡፡
ከታሪክም አንፃር ቤቱንም ከማቆየት ማዕዘን መታሰብ አለበት ያሉት የስራ ሀላፊው፣ ሲኒማ ኢትዮጵያን በተመለከተ የባህልና ቱሪዝም ራሱ፣ የከተማ አስተዳደሩ እና የሚመለከታቸው ሁሉ ቅርስ እንደሆነ ተረድተው የሚያደርጉትን ማወቅ አለባቸው ተብሏል፡፡

ምንጭ ፦ሸገር fm

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here