የፖሊቲካ አመጽና የሽብር አደጋ መድን አገልግሎት መስፋፋት የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ መልካም አጋጣሚ መፍጠሩ ተገለፀ

0
546

ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በተለያዩ አካባቢዎች ያስተናገደቻቸው የፖሊቲካ አለመረጋጋቶች ይህን መሰሉን የኢንሹራንስ አገልግሎት ፍላጎትን አሳድጓል።
የኢትዮጵያ የጠለፋ መድን ኩባንያ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወንድወሰን ኢተፋ፥ በሀገሪቱ በነበሩ አመጾች ንብረት የወደመባቸው ባለሀብቶች ካሳ ያላገኙት ለኢንቨስትመንቶቻቸው ዋስትና ስላልገቡ ሳይሆን ዋስትና የገቡት ለተለመዱት አደጋዎች ነበረ ብለዋል።
ሆኖም በሀገሪቱ የነበረው የፖለቲካ አለመረጋጋት የፖሊቲካ አመጽና የሽብር መድን ፍላጎትን አሳድጎታል ያሉት አቶ ወንድወሰን፥ በሀገሪቱ ያሉ የኢንሹራንስ ኩባንያዎችም አገልገሎቱን ወደ መስጠቱ እንዲገቡ አድርጓቸዋል ብለዋል።
አገልግሎቱን ከጀመሩት የኢንሹራነስ ኩባንያዎች ውስጥ የሚገኘው የኒያላ ኢንሹራንስ የማርኬቲንግና ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተገኝ ማስረሻ፥ ከ4 ዓመት በፊት የዚህ መድን አገልገሎት ተጠቃሚ አነስተኛ እንደነበር አስታውሰዋል።
ከጊዜ በሁዋላ የነበረው ሁኔታ ግን የፖለቲካ አለመረጋጋት የፖሊቲካ አመጽና የሽብር መድን ፍላጎትን ከፍ እንዳደረገው አቶ ተገኝ ተናግረዋል።
አሁን ላይ በሀገር ውስጥ ካሉ 17 የኢንሹራነስ ኩባንያዎች ጥቂት የማይባሉት የፖሊቲካ አመጽና የሽብር መድን አገልግሎትን መስጠት ጀምረዋል።

አሁን ላይ በሀገር ውስጥ ካሉ 17 የኢንሹራነስ ኩባንያዎች ጥቂት የማይባሉት የፖሊቲካ አመጽና የሽብር መድን አገልግሎትን መስጠት ጀምረዋል።
ሌሎቹ ደግሞ አገልገሎቱን ለመጀመር ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ጥያቄያቸውን አቅርበው ምላሽን እየጠበቁ ነው ።
ይህ አይነት የመድን አገልገሎት በስፋት መጀመሩ ሀገሪቱ የሽብር አደጋዎች ተጋላጭ ናት ብቻ የሚል ትርጉም የሚሰጥ ሳይሆን፤ ለኢነቨስተሮች ሙሉ የሆነ የስጋት ዋስትና በመስጠት የሀገሪቱን ለኢንቨስትመንት ምቹነት ያረጋግጣል የሚል ትርጓሜ የሚሰጥ በመሆኑ ነው ተብሏል።
አቶ ተገኝ እንደሚሉት ደግሞ የዚህን መድን አግልገሎት መጠየቅ በቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት የሚመጡ ባለሀብቶች መገለጫ ሆኗል ።
ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ኢንሹራንስ ኩባንያዎች አሁን ላይ በአመት የሚሰበስቡት አረቦን ወይን ፕሪሚየም 8 ቢሊየን ብር ማለፉን መረጃዎች ያሳያሉ።
በዘርፉ ላይ አንዲህ አይነት አዳዲስ አገልግሎቶችን መጨመራቸው ስራውን ከማሳደጉም በላይ የሀገሪቱን የኢንቨስተመንት ተመራጭነት ያሳድገዋል ተብሎ ይጠበቃል።

ምንጭ ፦ፋና

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here