በቀን ወደ ኢትዮጵያ የሚሻገሩ ኤርትራውያን ቁጥር ከ53 ወደ 390 አሻቅቧል

0
535

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን መረጃ እንደሚጠቁመው ሁለቱ አገሮች ድንበራቸውን በከፈቱ ማግሥት በቀን ወደ ኢትዮጵያ የሚሻገሩ ኤርትራውያን ቁጥር ከ53 ወደ 390 አሻቅቧል።

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበሮቻቸውን ከከፈቱበት ካለፈው መስከረም ጀምሮ 27,500 ኤርትራውያን በኢትዮጵያ ጥገኝነት ጠይቀዋል ። ከሰሜናዊ ኤርትራ ድንበር የተሻገሩ 24,000 ሰዎች በትግራይ ክልል በሚገኘው እንዳባጉና መጠለያ የስደተኝነት ማመልከቻ ማቅረባቸውን የአውሮጳ ኮሚሽን የሰብዓዊ ዕርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ ሰነድ ይጠቁማል። በሰነዱ መሰረት ሌሎች 3,500 ኤርትራውያን በአፋር ክልል ተመሳሳይ የተገን ጥያቄ አቅርበዋል። እስከ ባለፈው ነሐሴ ወር ድረስ ብቻ 174,000 ኤርትራውያን ስደተኞች በኢትዮጵያ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መሪዎች ለዓመታት ተዘግቶ የቆየውን ድንበር የከፈቱት ባለፈው መስከረም አንድ ቀን ነበር።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here