በጅማ ከተማ በተከሰተ የአፈር መንሸራተት የ3 ሰዎችን ህይወት አለፈ

0
470

በጅማ ከተማ በተከሰተ የአፈር መንሸራተት የ3 ሰዎችን ህይወት መለፉን ፖሊስ አስታወቀ።

የጅማ ከተማ ፖሊስ ጽህፈት ቤት የኮሙዩኒኬሽን ዲቪዚዮን ኃላፊ ኢንስፔክተር ገዛኸኝ አውግቻው እንደገለጹት አደጋው የደረሰው አንድ ሲኖትራክ የጭነት ተሽከርካሪ ትናንት ቀን አስር ሰዓት አካባቢ በቦቼ ቦሬ ቀበሌ ቺሻየር በተባለው ሰፈር የደፋው አፈር መኖሪያ ቤት ላይ በመደርመሱ ነው፡፡

አፈር ተደርምሶ የመኖሪያ ቤት በመጫን ባስከተለው አደጋ የ3 ሰዎችን ህይወት መጥፋቱ የተገለጸ ሲሆን፥ ከሟቾቹ መካከል የአንድ ቀን አራስ ከነልጇ እንደሚገኙበትም ገልጸዋል።

መኖሪያ ቤት አፈሩ ከተደፋበት ቦታ በቅርበት ዝቅተኛ ቦታ ላይ የነበረ በመሆኑና ለአደጋው መጋለጡን አመልክተዋል፡፡
የተደፋው አፈር ተደርምሶ ቤቱ ላይ አርፎ ባደረሰው አደጋም ከነልጇ ህይወቷ ያለፈው አራስ የ22 ዓመት ዕድሜ የነበራት መሆኑን ኢንስፔክተር ገዛኸኝ ተናግረዋል።የሟቿ ባለቤትም የአካልና የስነልቦና ጉዳት ደርሶበት በጅማ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገለት የሚገኝ ሲሆን፥ ሶስተኛውም ሟችም ህጻን ልጅ መሆኑ ታውቋል::

በአደጋው ቤቱ ከጥቅም ውጭ መሆኑን የገለጹት ኢንፔክተር አውግቸው አፈሩን የደፋው ሲኖትራኩ አሽከርካሪ ለጊዜው ቢሰወርም ፖለስ ክትትል እያደረገበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግህሎት ኤጄንሲ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here