ኢትዮ ቴሌኮም በዓለም አቀፍ ጥሪዎች እና የአጭር የፅሁፍ መልዕክት ዋጋ ላይ ቅናሽ ማድረጉን ገለፀ።

0
313

ኢትዮ ቴሌኮም በዓለም አቀፍ ጥሪዎች እና የአጭር የፅሁፍ መልዕክት ዋጋ ላይ ቅናሽ ማድረጉን ገለፀ።

ኩባንያው ዛሬ በሰጠው መግለጫ በዓለም አቀፍ የድምፅ ጥሪዎች ላይ ከ10 እስከ 40 በመቶ ቅናሽ ማድረጉን ነው ያመለከተው።በተጨማሪም በአጭር የፅሁፍ መልዕክት ላይ እስከ 51 በመቶ ቅናሽ አድርጓል።
በመግለጫው የዋጋ ቅናሹ በስድስት ዞኖች ተከፋፍሎ መደረጉም ተመልክቷል።
በዚህም መሰረት፦

በአፍሪካ- ቀደም ሲል በደቂቃ 10 ብር ከ29 ሳንቲም የነበረ ሲሆን፥ በቅናሹ 7 ብር ከ50 ሳንቲም፣
በእሲያና መካከለኛው ምስራቅ- በደቂቃ 8 ብር ከ63 ሳንቲም የነበረው 7 ብር ከ19 ሳንቲም፣
ሰሜን አሜሪካ- 8 ብር ከ63 ሳንቲም የነበረው 7 ብር ከ17 ሳንቲም፣
ደቡብ አሜሪካ- 10 ብር ከ29 ሳንቲም የነበረው 7 ብር ከ36 ሳንቲምና
ኦሺኒያ ደሴቶች- 23 ብር የነበረው 8 ብር ከ95 ሳንቲም ሆኖ ነው ቅናሽ የተደረገው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here