ብሔራዊ የሀዘን ቀን ታወጀ

0
384

ብሔራዊ የሀዘን ቀን ታወጀ

የቀድሞ ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ህልፈትን ተከትሎ ነገ ረብዑ ታህሳስ 10/ 2011 ዓ.ም የአንድ ቀን ብሄራዊ ሀዘን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ታውጇል፡፡

በብሔራዊ የሀዘን ቀኑ በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎችና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም በውጭ በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽሕፈት ቤቶች ለአንድ ቀን የሀገሪቱ ሰንደቅ አላማ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ ተወስኗል።
በተመሳሳይ ንብረትነታቸው የኢትዮጵያ የሆኑ መርከቦችም በነገው እለት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ባንዲራ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ የሚያደርጉ ይሆናል።

ምክር ቤቱ የሀዘን ቀኑን ያወጀው በዛሬው እለት ባካሄደው 4ኛ አመት የስራ ዘመን 12ኛ መደበኛ ስብሰባው ላይ ነው።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአዋጅ ቁጥር 653/2009 አንቀፅ 11 ላይ በተደነገገው መሰረት ነው በመላው ሀገሪቱ የ1 ቀን ብሄራዊ ሀዘን ያወጀው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here