የፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የአይን ብሌን ለኢትዮጵያ የአይን ባንክ ተለገሰ

0
878

የቀድሞ ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የአይን ብሌን ለኢትዮጵያ የአይን ባንክ ተለገሰ

የቀድሞ ፕሬዝዳንት በ12 አመት የፕሬዝዳንትነት ቆይታቸው የተለያዩ ሰብዓዊ ድጋፍ የሚሰጡ ተቋማትን በማቋቋም ይታወሳሉ።
ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ካቋቋሟቸው ተቋማት መካካል በ1995 ዓ.ም የተመሰረው የኢትዮጵያ የአይን ባንክ ይጠቀሳል።
በወቅቱ የአይን ባንኩን ከማቋቋም ባሻገር የአይን ብሌናቸውን ብርሃናቸውን ላጡት ወገኖች ለመለገስ ቃል ገብተው ነበር።
እናም የቀድሞ ፕሬዝዳንት ህይወታቸውን ማለፉን ተከትሎ በቤተሰቦቻቸው አማካኝነት የአይን ብሌናቸው መለገሱን የኢትዮጵያ የአይን ባንክ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ለምለም አየለ ገልጸዋል።

በ95 አመታቸው ያረፋት የቀድሞ ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስን የአይን ብሌናቸውን ለመለገስ ቃል የገቡ የመጀመሪያ ሰው መሆናቸውን የኢትዮጵያ የአይን ባንክ አስታውቋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here