አርቲስት ዳዊት ሰንበታ በአዲስ አልበም እየመጣ ነው

0
815

አርቲስት ዳዊት ሰንበታ በአዲስ አልበም እየመጣ ነው
“ስም የላትም” አዲስ አልበም
እየተገማሸረ እንደ ጅረት ውሃ የሚፈሠው ድምፁ ፍፁም መንፈስን የሚያረሠርስ ነው ይሉለታል፤ ሙዚቃዎቹን ያጣጣሙት።…የሙዚቃ መሳሪያን ያለ ድምፅ ሲጫወት ፤በሙዚቃ መሣሪያ ታጅቦም ድምፁን መስማት የቻሉ ሁሉ የማይረሡት ሁሌ አዲስና ጣዕም ያለው ነው።….
ዳዊትን ከሙዚቃ ጋር ያወዳጀው በተፈጥሮ የነበረው ክህሎት ሲሆን በትምህርትም ታግዞበታል፤በቫዬሊን ሜጀርና በፒያኖ ማይነር ከክፍሉ አንደኛ በመውጣት ከያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ዱፕሎማውን ይዞ በአሜሪካ ቦል እስቴት ዩንቨርስቲ የሙዚቃውን ትምህርት አክሎበታል።
ከዚያም ከዝነኛው ኢትዬ ስታር ባንድ ጋር ኦርጋኒስት በመሆን ከዝነኞች ድምፃዊያን ጋር ለስድት ዓመታት የተጫወተው አርቲስት ዳዊት ሰንበታ በሂልተን ሆቴል በሼባ ላውንጅ ባር ውስጥ “ዋን ማን ባንድ” (ብቻውን የኪቦርድ የሙዚቃ መሣሪያ እየተጫወተ) ድምፁን ይበልጥ አሟሸ ፤ ያኔ ገና ከጅምሩ የተዋጣለት ሆነ።
ከዛም በ1984 እና በ1992 ዓ.ም በታንጎና በኤሌክትራ ሙዚቃ አሣታሚዎች አማካኝነት ሁለት የሙዚቃ ቅንብር አልበሞችን አበርክቷል።
ዳዊትን መስማት የሚፈልጉና የሚያደንቁት ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ በኩሪፍቱ ዲፕሎማት ሬስቶራንት በሀርመኒይ ሆቴልና በሌሎችም እየሄዱ ብቻውን ኦርጋን እየተጫወተ ሲዘፍን ያዩታል።
ቮካል ሪከርድስ ይህን ታላቅ የሙዚቃ ሰው ከተናፋቂው ድምፁና ከተለየ አቀራረቡ ጋር የተዋህደውን “ስም የላትም” የተስኘውን ስለ እናት ውለታ ያቀነቀነበትና ሌሎችም አዳዲስ ስራዎቹን ሊያስደምጠን በቅርቡ ጠብቁ ይላል!
አልበሙ አስር ዘፈኖችን ያካተተ ሲሆን የሰባቱ ዘፈኖች የስንኝ ደራሲ ደግሞ ታዋቂው ይልማ ገ/አብ ነው።
የዳዊት ሰንበታ አዲስ የሙዚቃ ስራን ለማጣጣም ኦርጅናል ሲዲ በመግዛት እና እግረ መንገዶትንም የጥበብ አጋርነቶን ያሳዩ ይላል…..ቮካል ሪከርድስ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here