የቀድሞ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ አጭር የሕይወት ታሪክ

  0
  762

  ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደ ጊዮረጊሰ
  ከ1917-2011

  የቀድሞ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ታህሳስ 19 ቀን 1917 ዓ.ም ነበር በአዲስ አበባ ከተማ የተወለዱት።

  ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደ ጊዮረጊሰ ኢትዮጵያ ባስተናገደቻቸው የመጨረሻዎቹ ሶስት የመንግስት ስርአት ለውጥ ውስጥ በሁሉም ሀገራቸውን አገልግለዋል።
  የቀድሞ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ከ1994 እስከ 2006 ዓ.ም ድረስ ርዕሰ ብሔር ሆነው  ለ12 ዓመታት አገልግለዋል።
  ፕሬዚዳንቱ ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግስት ጀምሮ የፓርላማ አባል በመሆን ነበር ሀገርንና ህዝብን ማገልገል የጀመሩት።አቶ ግርማ በአጼ ሀይለስላሴ ዘመነ መንግስት በወታደርነት ውሰጥ አልፈው መቶ አለቃ እስከመሆን ደርሰዋል።
  በወታደርነት ዘመናቸውም አየር ሀይል ውስጥ ከመስራት ጀምሮ የኤርትራ ሲቪል አቪየሽን የበላይ አዛዥ ሆነው አገልግለዋል።
  በያኔው የንግድ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ውስጥ ጠቅላይ ዳይሬክተር ሆነውም ሰርተዋል።
  በ1953 ዓ.ም የፓርላማ አባል የሆኑት መቶ አለቃ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ በ52ኛው ዓለም አቀፍ የፓርላማ ስብሰባ ላይ ተቀዳሚ ፕሬዝዳንትም ሆነው የሀገራቸውን ልኡክ መርተዋል።
  በደርግ የመንግስትነት ዘመን የኤርትራን ችግር በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በተቋቋመው ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ነገሮችን ለማለሳለስ በብርቱ ጥረዋል ይላሉ በቅርብ የሚውቋቸው።
  በኤርትራ የቀይ መስቀል ማህበር ፕሬዝዳንትም ነበሩ።
  የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኦሮምኛ፣ አማርኛ፣ አፋርኛ፣ እንግሊዘኛ፣ ጣሊያንኛ እና ፈረንሳይኛ ቋንቋዎችን እንደሚችሉም ይነገራል።
  የአካባቢ ጥበቃ ጠንካራ ተቆርቋሪ ናቸው የሚባልላቸው እና በዚህም ለረጅም አመታት የሰሩት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ለም ለኢትዮጵያ በሚባል አካባቢ ጥበቃ ላይ በሚሰራ ማህበርም የቦርድ ፕሬዝዳንት ሆነው ሰርተዋል።
  በኢትዮጵያና ኤርትራ መሀል ሰላም እንዲመጣ ጊዚያቸውንና አቅማቸውን የሰጡ በሚልም ይሞገሳሉ።
  ከአስራዎቹ እድሜያቸው ጀምሮ ከሰባት አስርት አመታት በላይ ሀገራቸውን በወታደርነት ፣በከፍተኛ የመነግስት የስራ ሀላፊነትና ፕሬዝዳንትነት ያገለገሉት አቶ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ከ10 ቀን በኃላ 95ኛ አመታቸውን ይይዙ ነበር።

  የፕሬዚዳንት ግርማ ባለቤት ከአንድ ዓመት በፊት ማረፋቸው የሚታወስ ሲሆን  የአምስት ልጆች አባት ነበሩ።
  በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ላይ ረጅም አመታትን የተራመዱ፣ ጊዚያቸውን ለበጎ አገልግሎት በሰፊው ሰጥተዋል የሚባልላቸው የአንጋፋውና ባለታሪክ ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ቀብራቸው በመንግስታዊ ስነስርአት ይፈጸማል።

  LEAVE A REPLY

  Please enter your comment!
  Please enter your name here