የጥቆማ መስጫ ስልክ መስመሮች ይፋ ሆኑ!

0
505

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት በከተማው የሚታዩ የአገልግሎት አሰጣጥ ቅሬታዎች፣ በህገወጥ መንገድ ታጥሮ የተቀመጡ መሬቶች ፣ ህገወጥ የቀበሌ ቤቶች እና የኮንደሚኒየሞች እንዲሁም በአገልግሎት መስጫ ተቋማት እና የመንግስት መስሪያ ቤት ኃላፊዎች ወይም ሰራተኞች በአጠቃላይ በከተማው ውስጥ የሚከናወኑ ማንኛውንም ህግን ያልተከተሉ ሥራዎች ላይ ህብረተሰቡ ተሳትፎ እንዲያደርግ ይፈልጋል፡፡
የከንቲባ ፅ/ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪ ወ/ሪት ፌቨን ተሾመ በሰጡት መግለጫ ህብረተሰቡ በከተማው የሚስተዋለውን ደካማ አሰራር እና በብልሹ አሰራር የተዘፈቁ አመራሮችን እና ባለሙያዎችን እንዲጠቁሙ እና ለውጡን በመደገፍ የድርሻቸውን እንዲወጡ ለከተማዋ ነዋሪ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በጥቆማው ላይ ሊካተቱ ከሚገባቸው መረጃዎች ውስጥ ፦
1፦ የድርጊቱ አይነት፣
2፦ የኃላፊው ሙሉ ስም
3፦ የሰራተኛው ሙሉ ስም
4፦ የአገልግሎት ዘርፍ
የጥቆማ መስጫ የስልክ መስመሮች

የካ (+251 118548252 )
ንፋስስልክ (+251 118548067 )
ልደታ (+251 118547907 )
ኮልፌ (+251 118547896 )
ጨርቆስ (+251 118548753)
አዲስከተማ (+251 118548423 )
አራዳ (+251 118548397 )
አቃቂ (+251 118548257 )
ቦሌ (+251 118548415 )
ጉለሌ (+251 118548638 )
በመጠቀም ጥቆማ በማድረስ ለውጡን እንዲደግፉ የከንቲባ ፅ/ቤት ጥሪውን አቅርቧል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here