ኢትዮጵያውያን ወደ መካካለኛው ምስራቅ እንዳይሄዱ ዳግም ዕገዳ ተጣለ

0
391

የኢትዮጵያ መንግስት ዜጎቹ ወደ መካከለኛው ምስራቅ እንዳያመሩ ዳግም ዕገዳ መጣሉ ተሰምቷል ፡፡
ገልፍ ኒውስ እንዳስነበበው ኢትዮጵያውያን የቤት ሰራተኞች ካለፈው ሳመንት ጀምሮ ወደ መካካለኛው ምሰራቅ ሀገራት የሚያደርጉት ጉዞ ታግዷል ፡፡
ምክንያቱ ያልታወቀው የጉዞ ክልከላ የኢትዮጵያ መንግስት ከመካካለኛው ምስራቅ ሀገራት ጋር የስራ ስምሪት ስምምነት ባደረገ ማግስት መፈጠሩ እያነጋገረ ይገኛል ፡፡
መንግስት ለዓመታት በዜጎቼ ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እተፈጸመ ነው በሚል የጉዞ ዕገዳ ጥሎ ቢቆይም በቅርቡ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማጠናቀቅ የቤት ሰራተኞች ወደ መካካለኛው መስራቅ መሄድ እንደሚችሉ አስታውቆ ነበር ፡፡
በየቀኑ ወደ ተባባሩት አረብ ኤምሬትስ ብቻ ከአራት መቶ የሚበልጡ ኢትዮጵያውያን ለቤት ሰራተኝነት እንደሚያመሩ መረጃዎች ያሳያሉ ፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here