ሼክ አልአሙዲ በህይወት እንደሚገኙና በቅርቡም በሙስናና ጉቦ በመስጠት እንደሚከሰሱ ተገለፀ

0
741

ብሉምበርግ ስለ ሼክ አላሙዲን በአንድ ቀን ውስጥ ሁለተኛውን ዘገባ ይዞ የወጣ ሲሆን ሼክ መሐመድ አል አሙዲ በህይወት እንደሚገኙ እና እስካሁን በእስር ቤት መሆናቸውን በዘገባው አስታውቋል።
በሙስናና ጉቦ በመስጠት ተጠርጥረው እንደተያዙ የሚነገረው አላሙዲን በቅርቡም ክስ እንደሚሰረትባቸው ነው ብሉምበርግ ያስታወቀው።
ሼክ መሐመድ አል አሙዲ በእስር ላይ እያሉ ህይወታቸው አልፏል በሚል ለተሰራጨ መረጃም ማንነታቸው ያልተገለፀ የሳዑዲ አረቢያ ባለስልጣናት ሼክ አላሙዲን በይህወት እንዳሉ እና ቀኑ በግልጽ ባይታወቅም ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ አስታውቀዋል።
የሼክ መሐመድ አል አሙዲ ቃል አቀባይ ቲም ፔንድረይ እንደተናገሩት ከሆነ ሔክ አላሙዲን እስካሁን በምንም አይነት ጥፋት እንዳልተከሰሱ በመግለፅ፤ ሌላ መረጃ ግን ከመስጠት ተቆጥበዋል።
የሚድሮክ ኢትዮጵያ ሊቀ መንበር ሼክ መሐመድ አል አሙዲ በሳዑዲ ዓረቢያ በተጀመረው ፀረ ሙስና ዘመቻ ነበር ከዓመት በፊት በቁጥጥር ሥር የዋሉት።
በተለያዩ ጊዜያትም ከእስር ስለመለቀቃቸው ቢነገርም በተደጋጋሚ ውሸት ሲሆን ተስተውሏል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድም ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ በሳኡዲ አረቢያ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ሼክ መሐመድ አል አሙዲ እንደሚፈቱ ማረጋገጫ ተሰጥቶኛል ብለው የነበረ ቢሆንም፤ እስካሁን ግን ከእስር አልተለቀቁም።

አሁን ላይ የአላሙዲንን ንብረት እያስተዳደረ ያለው ወንድማቸው ሀሰን አላሙዲን ሲሆን ከታሰሩ ጀምሮ ሀብታቸው በስድስት ፐርሰንት ጨምሮ አሁን 8.3 ቢልዮን ዶላር አላቸው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here