በደቡብ ክልል የከፋ ዞን ምክር ቤት የዞኑን የክልልነት ጥያቄ በሙሉ ድምፅ አፀደቀ፡፡

0
589

የካፋ ዞን ምክር ቤት ዛሬ ኅዳር 6 ቀን 2011 ቀን 2011 ዓ.ም. ባደረገው ጉባዔ የካፋ ዞን የክልልነት ጥያቄን በሙሉ ድምፅ አጸደቀ፡፡
ዞኑ በተለይ ሰሞኑን ከቡና መገኛነት ጋር በተገናኘ በተፈጠረ ውዝግብ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ የነበረ ሲሆን፣ ለሳምንት ያክል በተካሄደ ሰላማዊ ሠልፍ ከተለፈፉ መፈክሮች መካከል የክልልነት ጥያቄ አንዱ ነበር፡፡
በዚህም ምክንያት፣ የዞኑ ምክር ቤት ጉባዔውን በማድረግ ውሳኔውን በሙሉ ድምፅ ተቀብሎ ማጽደቁ ታውቋል፡፡
በዞኑ መቀመጫ ቦንጋ ከተማ ወጣቶች ከፍተኛ የደስታ ሠልፎች እያደረጉ እንዳሉ እማኞች ከአካባቢው ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄ በደቡብ ክልል ምክር ቤት ተቀባይነት ማግኘቱን ተከትሎ በርካታ የክልሉ ዞኖች የክልልነት ጥያቄ እየተስተዋለባቸው ሲሆን፣ በዞን ምክር ቤቶች ደረጃም በአጀንዳነት ተይዞ ውይይት የተደረገባቸው ዞኖች አሉ፡፡

በተመሳሳይ ከንባታ ጠንባሮም የክልልነት ጥያቄ እያነሳ መሆኑ ታውቋል፡፡ በደቡብ ክልል ከዚህ ቀደም የሲዳማ እና ወላይታ ዞኖች የክልልነት ይገባኛል ውሳኔ አሳልፈዋል ፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here