አትሌት ደራርቱ ቱሉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆና ተሾመች

0
558

ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጊዜአዊ ፕሬዝዳንት ሆና ተሾመች።
ሰሞኑን ከፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንትነት ራሳቸውን በፈቃዳቸው በለቀቁት አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ ቦታ በውክልና የፌዴሬሽኑ ምክትል ተቀዳሚ ፕሬዝዳንት የሆነችውን ክብርት ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉን በፕሬዝዳንትነት ሰይሟል፡፡ይህም የሆነው ፌዴሬሽኑ ትናንት ማምሻውን በአካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ነው።
በዚህም መሰረት ጠቅላላ ጉባኤውን እስከሚያደርግ ባሉት ፌዴሬሽኑን በጊዜአዊ ፕሬዝዳንት ትመራለች።

በቀጣይ ሁለት ወራት ጊዜ ውስጥም ፌዴሬሽኑ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ በመጥራት ለቀሪዎቹ ሁለት ዓመታት የፌዴሬሽኑን ፕሬዚዳንት እንደሚያስመርጥ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here