ከስደተኝነት እስከ የኮንግሬስ አባልነት _ሶማሌ አሜሪካዊት ኢልሀን ዖማር

0
648

ትውልደ ሶማሌዪቱ አሜሪካዊት ኢልሀን ዖማር በአሜሪካ ኮንግረስ ምርጫ አሸንፋለች።
ዩናይትድ ስቴትስ  ውስጥ በፕሬዚዳንቱ የአራት ዓመት የሥልጣን ዘመን አጋማሽ፥ በተለምዶ በየአራት ዓመቱ ጥቅምት ወር ላይ በሚካሄደው ምርጫ (mid-term elections) የ37 ዓመቷ የሚኒሶታ የዲሞክራቶች ዕጩ ሶማሊያዊቷ ኢልሀን ዖማር አሸንፋለች። ትውልደ-አፍሪቃዊት ስደተኛ ኢልሀን የተወለደችው ሶማሊያ ውስጥ ነው። የልጅነት እድገቷን ያሳለፈችው በሶማሊያ እንዲሁም ለ4 አመታት በጎረቤት ኬንያ የስደተኞች መጠለያ ውስጥ ሲሆን በ14 አመቷ ደግሞ ከቤተሰቦቿ ጋር ወደ አሜሪካ በመሰደድ ኑሮዋን እዛው አድርጋለች።

የ3 ልጆች እናት የሆነችው ሶማሊያዊቷ ኢልሀን ዖማር ሪፐብሊካን ተፎካካሪዋን ጄኒፈር ዚይሊኒስኪን ያሸነፈችው 78,4 ከመቶ ድምጽ በማግኘት ነው። ኢህላም በሚኒሶታ ስታሸንፍ የመጀመሪያዊቷ ጥቁር ትውልደ-አፍሪቃዊት ብቻ ሳትሆን፤ የመጀመሪያዋ ሙስሊም ሴትም ናት። ያም ብቻ አይደለም በዩናይትድ ስቴትስ ኮንግሬስ የመጀመሪያዋ ሶማሊ አሜሪካዊትም ናት።

ከእርስ በእርስ ጦርነት ሽሽት ወደ አሜሪካ የተሰደደችው በኢትዮጵያ ጎረቤት የተወለደችው ትውልደ-ሶማሊያዊቷ ከስደተኝነት የኮንግሬስ አባልነት አስደናቂ ጉዞ በማድረግ በሀገረ-አሜሪካ ታሪክ ሠርታለች።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here