አዲሱ የፕሬስ ሴክሬታሪያት ዋና ስራዉ ለመገናኛ ብዙሃን መረጃዎችን ማድረስ እንደሆነ ተገለጸ

0
573

በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ስር የተቋቋመው ፕሬስ ሴክሬታሪ ጽ/ቤት  ቢልለኔ ስዩምን ሀላፊ፣  ሄለን የሱፍን ምክትላቸው አድርጎ የሾመ ሲሆን የቀድሞ የመንግሥት ኮሚኒኬሽንን ጽህፈት ቤትን ተክቶ  ከሚዲያ አካላት ጋር በቅርብ ለመስራት ማቀዱን አስታወቀ። ጽህፈት ቤታቸዉ ዋና ስራዉ በግልጽ ለመገናኛ ብዙሃን መረጃዎችን በፍጥነት ማድረስ መሆኑን አስገንዝበዋል።ሴክሬታሪያቱ  ለጋዜጠኞች በሰጠው የመጀመሪያ መግለጫው እስከ 2012 ዓም ድረስ መንግሥት በተግባር ሊተረጉመው ስለወጠነው እቅድ ማብራሪያ ሰጥቷል። የመንግስትን እቅድ በግልጽ ቋንቋ ለህዝብ ለማድረስ ያለመ ነው ስለተባለለት የዕቅድ ሰሌዳም /ዳሽቦርድ/ ገለጻ አድርገዋል። መንግስት ሊቀርፋቸው ያሰባቸው የዴሞክራሲ እጦትና ደካማ የፍትህ እጦት፣ ደካማ የመንግስት አገልግሎት አስጣጥ፣ ከፍተኛ የወጣቶች ስራ አጥነት፣ ያልተሟላ የትምህርት ጥራት፣ ሕገ ወጥነት እና ስርዓተ አልበኝነት የሚሉ ነጥቦች በዕቅድ ሰሌዳው ከተካተቱት ዉስጥ እንደሚገኙበትም ወ/ሮ ቢልለኔ ስዩም አብራርተዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here