ጋዜጠኛ ጀማል ካሺጊን የበላው ጅብ ምነዉ አልጮህ አለ

0
815

 

የ60 አምቱ ሳውዲ አረቢያው ጋዜጠኛ ጀማል ካሺጊ  አንዲት ወረቀት እንዲሰጠው ለመጠየቅ ከገባበት የሳውዲ ኤምባሲ እንደ ዘበት ቀልጦ መቅረቱ እጅግ አነጋጋሪ ሆኗል። የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊን ለመግደል ስያቅድ እንደነበር ተገለፃል፡፡
በዚህም ቱርክ በሚገኘው የሳውዲ ቆንስላ ውስጥ 15 ልዩ ቡድኖችን አሰማርታ ግድያውን ፈጽማለች ተብሏል፡፡

ጋዜጠኛ ጀማል የሳውዲ መንግስትን በመንቀፍ የሚታወቅ ሲሆን ለዋሽንግተን ፖስትና ለሌሎችም ጋዜጦች ይጽፋ ነበር::በጽሁፎቹና በትችቶቹ የሳውዲ መንግስትን ሲያበሳጭ ኑሮአል። ጋዜጠኛውም ለህይወቱ በመስጋት አሜሪካ ውስጥ የመኖሪያ ፈቃድ (ግሪን ካርድ) ተሰጥቶት እየኖረም ነበር።

በቅርቡ የቱርክ ዜግነት ያላትን እጮኛውን ለማግባትና ጋብቻውን ህጋዊ ለማድረግ ከቀድሞ የሳውዲ ዜግነት ካላት ሚስቱ ጋር ፍቺውን ለማድረግ የሚረዳውን ወረቀት ቢጠይቅ፣ መጥተህ ውሰድ በመባሉ ነበር አንካራ ቱርክ የሚገኘው የሳውዲ እምባሲ የገባው። ግን አልወጣም። ውጭ የምትጠብቀው አዲሲቱ ሚስቱ በሩ ላይ እየጠበቀች ቀረች እንጂ።
ጋዜጠኛው ሲገባ፣ “ድንገት ካልወጣሁ፣ ለቱርክና ለአሜሪካ ባለሥልጣናት ደውለሽ ንገሪ” ብሏት ነበር። እሷም ይህንኑ አደረገች።

የቱርክ ባለሥልጣናት “እንዴት አገራችን ውስጥ እንዲህ ይደረጋል” ሲሉ ገብተን እንፈትሽ ሲሉ ዶናልድ ትራምፕን ጨምሮ የአሜሪካ ባለስልጣናት “ሳውዲ ለዚህ እንቆቅልሽ መልስ ስጪ” እያሉ ነው። የኒውዮርክ ታይምስ  ዘገባ ደግሞ ጋዜጠኛው እምባሲ እንደሚመጣ ከታወቀ  ጊዜ ጀምሮ ሳውዲዎች 15 ነፍሰ ገዳዮችን ልከው  እምባሲ ውስጥ እየጠበቁት ነበር እዚያው ገድለውታል ብሏል።ይህ 15 አባላት ያሉት ቡድን ግድያውን ከፈጸመ ከሁለት ሰዓታት በኋላ አንካራን ለቆ ወደ ተለያዩ ሀገራት ማቅናቱን ኒውዮርክ ታይምስ የቱርክ ባለስልጣናትን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

አሁን ቱርክና ሳውዲ፣ አሜሪካና ሳውዲ ፣ እንዲሁም የዓለም የንግግርና ሃሳብን የመግለጽ መብት ተከራካሪዎችና ከሳውዲ ጋር ተፋጠዋል።

እውነት ጋዜጠኛ ጀማል ካሺጊን የበላው ጅብ የሚጮኸው መቼ ነው?

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here