ለመጀመሪያ ጊዜ የ’ሰላም ሚኒስቴር’ ተቋም በአገራችን ሊቋቋም ነዉ

0
756

የ’ሰላም ሚኒስቴር’ በአገር ውስጥ ሰላም እና የሕግ የበላይነት ላይ ይሰራል ሲል ጠ/ሚኒስቴር ጽ/ቤት ገልጻል

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ “የሰላም ሚኒስቴር” የተባለ አዲስ ተቋም እንዲቋቋም በረቂቅ አዋጁ ላይ ማካተቱ ይታወሳል።

ለመጀመሪያ ጊዜ የሚቋቋመው የ’ሰላም ሚኒስቴር’ ተቋም በአገር ውስጥ ሰላም እና የሕግ የበላይነት እንዲሰፍን የሚሰራ መሆኑን ጠ/ሚኒስቴር ጽ/ቤት ገለጾል፡፡

የጠ/ሚኒስቴር ጽ/ቤት ሚኒስቴር ልዩ ሃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ እንደገለጹት አዲስ የሚቋቋመው የሰላም ሚኒስቴር በሕዝቡ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ በጋራ መገንባት እንዲቻል ትኩረት ይሰጣል።

በፖሊሲ ደረጃ ሰላምን በዋና አጀንዳነት የሚመራ ተቋም ያስፈልጋል ተብሎ በመታመኑ እንዲቋቋም መወሰኑንም አቶ ፍጹም ገልጸዋል።

የ”ሰላም ሚኒስቴር” ሰላም ላይ ያተኮሩ የተለያዩ ተግባራትን በማቀናጀት የሚመራ ይሆናል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ “የሰላም ሚኒስቴር” የተባለ አዲስ ተቋም እንዲቋቋም በረቂቅ አዋጁ ላይ ማካተቱ ይታወሳል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here