በዘንድሮው በጀት አመት ለቅርስና ጥበቃ ባለስልጣን ከተመደበው 29 ሚሊዮን ብር፤ 20 ሚሊዮኑን ለላሊበላ ተመድቦል

0
712

 

ኢትዮጵያን ከሚጎበኙ ቱሪስቶች አብዛኞቹ ላሊበላን ይጎበኛሉ። ከጎብኚዎቹ የሚገኘው ገቢም ቀላል አይደለም።የሚያስገኘው ገቢና የተሰጠው ትኩረት ግን አይመጣጠንም ለዚህ ተጠያቂዉ ደግሞ የኢትዮጵያ መንግስት ብቻ ሳይሆን ዩኔስኮንም ጭምር ነው ይላሉ የቅርስ ጥበቃ ባለሙያዎች

የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ከተፈጥሯዊ አደጋ ለመከላከል በሚል ግዙፍ የብረት ምሰሶ በቤተክርስቲያኖቹ ጣሪያ ከተተከለ ዓመታት ተቆጠረዋል።ሆኖም ምሰሶው እንደታሰበው ቅርሱን ከአደጋ የሚከላለል ሳይሆን፤ እያደር ቅርሱን የሚደመስስ ሆነ። ይህንን ያስተዋሉ የላሊበላ ነዋሪዎችም የሰሚ ያለህ እያሉ ነው። የቅርስ ጥገና እውቀት የሌላቸው ግለሰቦች በመዶሻና በመሮ አብያተ ክርስቲያናቱን አጎሳቁለዋል። አስከትሎም ቅርሶቹ ላይ አንዴ የቆርቆሮ ሌላ ጊዜ ደግሞ የእንጨት ጣሪያ ተደርጎ ጫና ደርሶባቸዋል።
ከዚህ ቀደም የተሰሩ ጥናቶችም ቅርሱ ሊጠፋ ስለመቃረቡ ማስረጃ አቅርበዋል። አሳሳቢ ደረጃ ላይ ከሚገኙት መካከል ቤተ መድኃኔአለም ይገኝበታል። በቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን አማካይነት ቤተ ገብርኤል ሩፋኤል እንዲሁም ቤተ ጎለጎታ ተጠግነው ጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኙ ሲሆን የተቀሩት ቅርሶችም ሳይውል ሳያድር መፍትሄ እንደሚሹ ይጠቁማሉ።

አጠቃላይ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ለመጠገን ለዩኔስኮ ያቀረበዉ ፕሮጀክት ተቀባይነት አግኝቷል።  አብያተ ክርስቲያናቱን ለማደስ 300 ሚሊዮን ብር በጀት ያስፈልጋል።

በዘንድሮው በጀት አመትም ለቅርስና ጥበቃ ባለስልጣን ከተመደበው 29 ሚሊዮን ብር፤ 20 ሚሊዮኑን ለላሊበላ እንደመደቡ ዳይሬክተሩ ገልጸው፤ ለእድሳት የሚሆነውን ገንዘብ እስካገኙ ድረስ ስራውን ከማስጀመር ወደኋላ እንደማይሉ የቅርስ ትንትና ትበቃ ባለስልታን ይገልጻል።

የቅርስ ተቆርቋሪ ማህበረሰብ ጥያቄ ግን የላሊበላ አብያተ ክርስትያናትን ለመታደግ በቂ ጊዜ የለንም አደጋ ዉስት ነን የሚል ነዉ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here