ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እና ለቲም ለማ መታሰቢያ የሚሆን “ONE ETHIOPIA-UNITED WE STAND” የሚል ዶክመንታሪ በሆሊዉድ የፊልም ባለሙያ ተዘጋጀ

0
1097

ከኢትዮጰያዊ አባትና ከአሜሪካዊ እናት የተወለደችዉ ንግስት ሰናይ ልኬ የታዋቂዉ አብዮተኛና የነፃነት ታጋይ የዶ/ር ሰናይ ልኬ ልጅ ነች::በሆሊዉድ የፊልም ዳይሬክተር ጸሀፊና ፕሮዲዉሰር የሆነችዉ ንግስት ሰናይ በ “Phat Girlz “እና “Ben & Ara ” በተሰኙት ፊልሞቿ በይበልጥ ትታወቃለች።
በአብዛኛዉ የአፍሪካ አንደነትንና ታሪክን የሚዳስሱት ፊልሞቿ አለም አቀፍ ሽለማቶችን አግኝታባቸዋለች።
የኢትዮጰያን ታሪክ በሰፊዉ በፊልሞቼ ማሳየት እፈልጋለሁ የምትለዉ ንግስት “እኔ ከአንድ ብሄር የመጣሁ ቢሆንም ከብሄሬ በፊት ግን በቅድሚያ ኢትዮጰያዊ ነኝ፤ሁሉም ብሄር በኢትዮጰያ ጥላ ስር አንድነቱ ተጠናክሮ የማየት ምኞት አለኝ ይህንን ስሜት ለማምጣት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እና ቲም ለማ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ አስደሳች ነዉ” ትላለች ለእነሱ መታሰቢያ የሚሆንም ” ONE ETHIOPIA-UNITED WE STAND”የሚል ዶክመንታሪ ያዘጋጀች ሲሆን እሱን ለማሳየትም ወደ ኢትዩጰያ መጣለች።
ለኢትዮጽያ አሁን ጥሩ ጊዜ እንደሆነ ይሰማኛል ስለዚህ ሁሉም አነድነትን የሚያጠናክሩ ስራወችን ከሰራ በጥቂት አመታት ዉስጥ ትለቅ ህዝቦች አንሆናለን ትላለች ንግስት ሰናይ ልኬ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here