ኤርትራ ከኢትዮጵያ በፌዴሬሽን ስትቀላቀል ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ከተናገሩት

0
541

‹‹ዛሬ በወንድማማችነት የተቀላቀላችሁ ታማኞቻችን እናንተ የኢትዮጵያ የኤርትራ ተወላጆች ዜጎቻችን፣ እኛ በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥትነታችን፣ የኤርትራንና የኢትዮጵያን በፌዴራሲዮን መቀላቀል ዛሬ ለታማኝ ዜጎቻችን የምንገልጽበት ጊዜ ታሪካዊ የሆነ ሰዓት ነው፡፡ ይህንን ቀን አባቶቻችንና አባቶቻችሁ ለማየት ተመኙ፣ አልቻሉም፡፡ ለመስማትም ተመኙ አልሆነላቸውም፡፡ እኛና እናንተ ግን ለማየትም ልንደርስበትም ስለቻልን ታላቅ ዕድል አገኘን፡፡››
ይህንን ኃይለ ቃል ከስድሳ ስድስት ዓመታት በፊት መስከረም 11 ቀን 1952 ዓ.ም. ኤርትራ ከኢትዮጵያ በፌዴሬሽን ስትቀላቀል፣ ንጉሠ ነገሥቱ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የኤርትራን ፌዴራል አክት ሲያፀድቁ ያሰሙት ዲስኩር እንደነበር የሚተርከው ከዓመታት በፊት በታተመው የዘውዴ ረታ ‹‹በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት የኤርትራ ጉዳይ እ.ኤ.አ.1941-1963›› መጽሐፍ ነበር፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here