‹‹የኤርትራ ጉዳይ›› መጽሐፍ በሲዲ ቀረበ ::

0
861

በንባብ የቀረቡ ሥራዎች መልሰው በሌላ ሰው ሲተረኩ ወይም ሲደመጡ አዲስና ሌላ መልክ ይይዛሉ፡፡ተፍታተው ግልጽ ያልሆኑ ወይም ተፍታተው ያልገቡ ሐሳቦች ተተርከው ሲደመጡ እንዲህ ነበር እንዴ ያስብላሉ፡፡ የማድመጥ ዝንባሌ ላላቸውም ሆነ ለሌላውም የታሪክ መጽሐፎች በሲዲ (ኦዲዮ ቡክ) የሚቀርቡ ከሆነ አዲሱ ትውልድ ስለ አገሩ በወጉ ለማወቅ ይረዳዋል፡፡ እየተንቀሳቀሱ መኪና ዉስጥ ወይም ሌላ ቦታ ሆኖ መጽሐፉን በቀላሉ ለመረዳት ያስችላል።

ጋዜጠኛ፣ ዲፕሎማትና ስመጥር የታሪክ ጸሐፊ የነበሩት ዘውዴ ረታ (1927– 2008) ‹‹በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ኃይለ መንግሥት የኤርትራ ጉዳይ 1941-1963››የተሰነ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዲስኩርንና 554 ገጾች ያሉትን መጽሐፍ ለአድማጮች ይሆን ዘንድ፣ በከያኒው ተፈሪ ዓለሙ ተራኪነት፣ በኦዲዮ ሲድ ተዘጋጀተል፣ የ30 ሰዓታት ትረካም አለው፣ በትረካው ሥር የሚሰማውን የሙዚቃ ድርሰት ደግሞ በሙዚቀኛ ምንተስኖት ደምሴ የተዘጋጀ ነው።

የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ሕገ መንግሥቱ ከተሻሻለበት ከ1948 ዓ.ም. በኋላ የነበረውን በለውጥ የታጀበው ዘመን የሚያወሳውን መጽሐፍ ለማዘጋጀት በተለይ በለንደን፣ ፓሪስና ሮም ኢትዮጵያን የሚመለከቱ ስለ ዘመነ ኃይለ ሥላሴ የሚያወሱ ሚስጥራዊ ሰነዶች በቅርቡ ክፍት መሆናቸውን ተከትሎ፣ ጥናትና ምርምር ለማድረግ በተጓዙበት ለንደን ከተማ መስከረም 26 ቀን 2008 ዓ.ም. በድንገት ማረፋቸው ይታወሳል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here