በአዲስ አበባ ተማሪዎችን ሊያግዝ የሚችል የሱቅ ባንክ አገልግሎት በስፋት ሊጀመር ነው

0
507

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ያግዛል የተባለው የኤሌክትሮኒክስ ገንዘብ ማስተላለፍና መቀበል አገልግሎት ኢ-ገንዘብ ይባላል፡፡
ይኸው ተቋም ከሁሉም ባንኮች ጋር በወኪልነት የሚሰራ የመጀመሪያ ድርጅት ነው ፡፡
ኢ-ገንዘብ በሁለት ሰው የተቋቋመና 10 ሚሊዮን ብር ካፒታል ይዞ እንደተመሰረተ ሰምተናል፡፡
አንድ ተማሪ ከ30 ብር አንስቶ እስከ 6 ሺ ብር ድረስ ከአካባቢው ሳይርቅ ተቀማጭ ገንዘብ የማውጣትና ሌላም የባንክ አገልግሎት እንዲያገኝ ያግዘዋል ፡፡
ድርጅቱ ከሌሎች ትልልቅ ኩባንያዎች ጋርም ይሰራል ፡፡
በኢትዮጵያ በተለያዩ ገጠራማ አካባቢዎች ከወረቀት ጋር የተቆራኘውን የገንዘብ አጠቃቀም ወደ ዲጂታል ለመቀየርም እንደሚሰራ ተነግሯል፡፡
ብሔራዊ ባንክም ይህንኑ ዓላማ ይደግፋል የተባለ ሲሆን መንግስትም ብር ለማሳተም የሚያወጣውን የውጭ ምንዛሬ ይቀንስለታል፡፡
በኢትዮጵያ የሚገኙ 44 ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እና በሁሉም 154 ካምፓሶች ይኸው የሱቅ ገንዘብ አገልግሎት በቅርቡ ይጀመራል ፡፡
አሁን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ6 ኪሎ ካምፓስ አገልግሎቱ እንደተጀመረ ሰምተናል፡፡
አገር በቀል የሆነው ድርጅት ከትልልቅ ኩባንያዎች ጋር ከመስራቱም በተጨማሪ ለገጠርና ለከተማው ነዋሪ፣ ለኢንዱስትሪና ለሌሎችም ተጠቃሚዎች አገልግሎት የሚሰጥበት እቅድ ለው ፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here