መስከረም ሁለት ሲታወስ

0
614

መስከረም ሁለት ሲታወስ ልክ እንደ ሰልፉ በትርኢት መልክ የሚያልፉ ትውስታዎች፣ የዛሬዋን ሰሜን ኮሪያ አይነት ያሸበረቁ ሰልፎች የሚመስሉ ትእይንቶቸ ወደ አእምሮ ያመጣል፣

እንደው ከብዙ ሰወ አእምሮ ከማይጠፉት መሃል በቀበሌ እና አብዮት ጥበቃ ህዝቡ ሰልፍ እንዲወጣ የሚያደርጉት ማዋከብ፣ ያንን መመሪያ ተከትሎ በቀበሌ ቀመንበሮች መሪነት በሰልፍ ወደ አብዮት አደባባይ የሚተምም ስትር ያለ የህዝብ ሰልፍ፣ የአድአ ፓስታ እና መኮረኒ፣ የአቃቂ ብረታብረት እና ከሌሎች እልፍ ፋብሪካዎች የተውጣጡ የምርት መሳሪያዎቻቸውን በኩራት እየሳዩ የሚያልፉ ወዛደሮች፣ ፣ በነጭ አቡጀዲ ላይ በደማቅ ቀይ የተጻፉ ቢሮከራሲያዊ ካፓታሊዝምን፣ ኢምፔሪያሊዝምን፣ ፊውዳሊዘምን የሚያወግዙ መፈክሮች የያዙ የተላያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በሰሜት የተሞላ ሰልፍ፣

ሩሲያ ሰራሽ ታንኮች እና ብረት ለበስ ተሸከርካሪዎች ትርኢት፣ የጦሩ የተለያዩ ክፍሎች ወታደራዊ ሰልፎች ፣ ጓድ ሊቀመንበር አብዮቱን ለመቀልበስ የአድህሮት ኃይሎች ከውስጥ እና ከውጭ በአብዮቱ ላይ የሚሸርቡትን ደባዎችን በቆራጥነት ሰለመታገል ፣ አብዮታዊ ሰራዊታችን በሰሜን ግንባር ገንጣይ እና አስገንጣይ ሀይሎችን የገቡበት ገብቶ ለመደምሰስ እየከፈለ ስላለው መስዋእትነት በአስገምጋሚው ድምጻቸው የሚያደርጉት ለሰአታት የሚዘልቅ ንግግር ፣ የወዳጅ ሀገር መሪዎች ሌላ ረጅም ንግግር፣ የህዝባዊ ድርጅቶች የድጋፍ ንግግሮች……. የንግገሮቹ መርዘም እና መደጋጋም በጸሀይ የሚንቃቃው ታዳሚን ትእግስት የሚፈታተን መሆን አይረሳም፣

ደሞ ያ ድካም ሳይበቃ ታሪክ ሰሪ ነህ የሚባለው ሰፊው ህዝብ ግራ ክንዱ እስኪገነጠል እና ላንቃው አስኪላቀቅ ድረስ ጸረ እብዮተኞች ይውደሙ፣ አብዮቱ በጸረ አብዮተኞች መቃብር ላይ ያብባል.፣ ህብረተሰባዊት ኢትየጵያን እንገነባለን፣ ማሌ መመሪያችን ነው እና ሌሎች መፈክሮችን በስሜት ያስተጋባል፣

መስለረም ሁለት ብዙ ሊወራለት የሚችሉ ትዝታዎች አሉት፣ የፕሮፓጋንዳው ግለት ሶሻሊስታዊት ኢትዮጵያን በሀይል የመፍጠር ጥረቶች እና ክሽፈቶችን በደንብ የሚያሳይ ነበር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here