አልኮል በትንሹም ቢሆን መቅመስ ጤናን ይጎዳል- ጥናት

0
3295

ቆየት ያሉ ጥናቶች በየዕለቱ ለሴቶች አንድ ለወንዶች ሁለት መጠጥ መጠጣት የልብ በሽታን ይከላከላል ሲሉ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡ ሆኖም አዳዲስ ጥናቶች ይህንን ድምዳሜ የሚያፈርሱ ሆነዋል:: በታዋቂው የህክምና ምርምር ውጤቶች መጽሄት ላንሴት ላይ The Global Burden of Disease  የተባለ ጥናት እንዳመለከተው መጠጥ መቅመስ የልብ ህመምን በመከላከል መጠነኛ ጠቀሜታ ያለው ቢሆንም ልካንስር እና ሌሎች የጤና ችግሮችን በማጋለጥ የሚያመጣው ችግር እንደሚልቅ ይገልጻል::

ተመራማሪዎቹ በጥናታቸውም ቢያንስ በቀን አንድ የሚጎነጩ ሰዎች መጠጥ ከማይቀምሱት ይልቅ ከአልኮል ጋር ተያያዥነት ባላቸው 23 በሽታዎች የመያዝ ዕድላቸው በዜሮ ነጥብ አምስት ከፍ እንደሚል አስታውቀዋል፡፡

ተመራማሪዎቹ በዚህ ጥናት ላይ 28 ሚሊየን የሚደርሱ ተሳታፊዎች የተካፈሉባቸው 592 የተለያዩ ዓለም አቀፍ ጥናቶችን አገላብጠዋል፡፡

አላማቸውም ከአልኮል ጋር በተያያዘ የዓለም ስጋት እየሆነ የመጡ በሽታዎችን ሁኔታ ለመለያት እንዲያስችላቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በዓለማችን 2 ነጥብ 4 ቢሊየን ወይንም አንድ ሦስተኛው የዓለም ህዝብ መጠጥ ይጎነጫል ያሉ ሲሆን ከነዚህም መካከል 2 ነጥብ 2 ሴቶች እና 6 ነጥብ 8 የሚሆኑ ሴቶች ከመጠጥ ጋር በተያያዙ በሽታዎች ህይወታቸው እንደሚያልፍ በጥናታቸው አረጋግጠዋል፡፡

በዚህ መሰረትም ተመራማሪዎቹ በ2016 የተደረጉ ጥናቶችን በመንተራስ በዓለማችን የሰው ህይወት በመቅጠፍ አልኮልን ሰባተኛ ደረጃ ላይ አስቀምጠውታል፡፡

በየሀገሩ ያለው መጠጥ የመውስድ ባህል እንደየአካባቢው የሚለያይ ሲሆን ተመራማሪዎቹ በዴንማርክ 95 በመቶ ሴቶች 97 በመቶ ደግሞ ወንዶች መጠጥ ይጎነጫሉ በማለት የመጀመሪያ ደረጃ ላይ አስፍረዋቸዋል፡፡

ፓኪስታናውያንና ባንግላዴሻውያን በአንጻሩ ከአንድ በመቶ በታች የሆኑት ብቻ ናቸው አልኮል የሚወስዱት በማለት የመጨረሻ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

በሮማንያ የሚገኙት ወንዶች ደግሞ 8 ነጥብ 2 እንዲሁም በዩክሬን የሚገኙ ሴቶች 4 ነጥብ 2 አልኮል በመጎንጨት ቀዳሚዎቹ ናቸው ተብሏል፡፡

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here